March 21, 2019

የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኦዴግ) ከኢትዮጲያ መንግስት ጋር ያደረገውን ንግግር ኣስመልክቶ መግለጫ

Official ODF Logo

የኢትዮጵያ መንግሥት ከፍተኛ ልኡካን እና የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር አመራር አባላት በሀገሪቷ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ እየተስተዋሉ የመጡ የማሻሸያ ለውጦችን አስመልክቶ ከግንቦት 3-4፣ 2010 ዓም ውይይት ኣካሄደዋል። የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር በቆየ ፅኑ አቋሙ በመመስረት እነዚህ የማሻሸያ እርምጃዎች እንዲሰፉ፣ እንዲገለብቱና ፣ ጥልቀት እንዲኖራቸው ያለውን ፍላጎት በድጋሜ ያረጋግጣል። የኢትዮጵያ መንግሥት ልኡካን በበኩሉ በሰላማዊ መንገድ ከሚታገሉት ሁሉ ጋር ለመወያየትና ለመደራደር ያለውን ዝግጅትና ቁርጠኝነት ኣብስሯል። ሁለቱም ልኡካን ከኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኦዴግ) ጋር የተጀመረው ውይይት ለሰፊ ውይይት ፈር ቀዳጅ መሆኑን ኣስምረውበታል። ገና ብዙ የሚቀር ቢሆንም፣ ኦዴግ በቅርቡ በኢትዮጵያ መንግሥት በተወሰዱት የማሻሸያና የለውጥ እርምጃች ተበራቷል። በዚህም መሠረት እውነተኛ ፍትሓዊና ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት በሃገራችን ዕውን እንዲሆን የሚመኙ በሃገር ቤትም ሆነ…

Read More

በ”የሶማሌ ክልል ልዩ ፖሊስ” አማካይነት በኦሮሚያ እና በኦሮሞ ሕዝብ ላይ የተፈፀመዉን ወረራ በማስመልከት ከኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባር የተሰጠ መግለጫ

Official ODF Logo

ባለፉት ሦስት ዓመታት ዉስጥ በሕወሐት የሚመራዉና ለስሙ “የኢትዮጵያ መንግሥት ነኝ” የሚለዉ ገዢ ቡድን የተስፋፊዉን የሶሚሊያ መንግሥት የ“ታላቋ ሶማሊያ” ምሥረታ ህልም ዕዉን ለማድረግ እንደሚሠራ የሚያመለክቱ የተለያዩ ደባዎችን “አስተዳድረዋለሁ” በሚለዉ የኦሮሞ ሕዝብ ለይ እየፈፀመ መሆኑን በግልፅ አሣይቷል፡፡ እንደሚታወቀዉ የኦሮሚያን መሬት እና ሌሎች የአካባቢዉ ግዛቶችን አጠቃሎ “ታላቋን ሶማሊያ“ የመመሥረት ሙከራ የተጀመረዉ በዚያድባሬ ዘመነ መንግሥት ነበር፡፡ የ“ታላቋ ሶማሊያ” ምሥረታ እንቅስቃሴ በኢትዮጵያ፣ በኬንያ እና በጂቡቲ ግዛቶቸ ዉስጥ የሚኖሩትን የሶማሊኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች በወታደራዊ ኃይል በማንበርከክ እነዚህ ሕዝቦች የሰፈሩበትን መሬት ወደ ሶማሊያ ግዛት ለማጠቃለል የታለመ እንደነበረ አይዘነጋም፡፡ ይህ የ“ታላቋ ሶማሊያ” ህልም እንግዲህ በምሥራቅና ምዕራብ ሐረርጌ፣ በባሌ፣ በአርሲ፣ በጉጂ እና በቦረና የሚኖሩትን የኦሮሞ ብሔር አባላት እስከነመሬታቸዉ “ሶማሌ አቦ“…

Read More

የኢትዮጵያ አገራዊ ንቅናቄ ምሥረታ መግለጫ

coalition

የኢትዮጵያ አገራዊ ንቅናቄ ምሥረታ መግለጫ የኢትዮጵያ ሕዝቦች ለነፃነት፣ ለዲሞክራሲና ለፍትህ የሚያደርጉት ትግል እጅግ ወሳኝ ወደሆነ ደረጃ እየተሸጋገረ መሆኑን ሁላችንም የምንገነዘበዉ ነዉ፡፡ በሕወሐት ግፈኛ አገዛዝ ሥር ላለፉት ሃያ-አምስት ዓመታት በሕዝቦቻችን ላይ የወረደዉ ግፍና መከራ ከልክ በማለፉ የተቀጣጠለዉና ላለፈዉ አንድ ዓመት ካለማቋረጥ የቀጠለዉ የእምቢተኝነትና የአልገዛም ባይነት ሕዝባዊ የተቃዉሞ ትግል ለዓመታት ሲካሄድ የቆየዉ የኢትዮጵያ ሕዝቦች ትግል አዲስ ምዕራፍ ላይ መድረስ መገለጫ ነዉ፡፡ በዚህ ዛሬም ድረስ እየተካሄደ ባለዉ ሕዝባዊ እምቢተኝነት ምክንያት በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ዳግም በመስቀለኛ መንገዶች ላይ ትገኛለች፡፡ በአንድ በኩል መሠረታዊ የሆነ የሥርዓት ለዉጥ የሚፈልጉ ሕዝቦች እስከ አፍንጫዉ ከታጠቀ ጨካኝ የገዢ ቡድን ጋር የሞት ሽረት ትግል የሚያደርጉበት፤ በሌላ በኩል ሕወሐት መራሹ ቡድን በመሣሪያ…

Read More

ከኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባርና ከአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ የወቅቱን የኢትዮጵያ ሁኔታ በማስመልከት የተሰጠ መግለጫና ለሁሉም ነፃነት ፈላጊ ወገኖች የቀረበ ጥሪ

Official ODF Logo

ኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባርና ከአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ የወቅቱን የኢትዮጵያ ሁኔታ በማስመልከት የተሰጠ መግለጫና ለሁሉም ነፃነት ፈላጊ ወገኖች የቀረበ ጥሪ የኢትዮጵያ ሕዝቦች ለነፃነት፣ ለፍትህ፣ ለእኩልነትና ለትክክለኛ ዲሞክራሲ የሚያደርጉት የብዙ ሺህ ንፁሃን ዜጎችን የሕይወት መስዋዕትነት የጠየቀ የተቃዉሞ እንቅስቃሴ ተጠናክሮ ከመቀጠልም አልፎ ወደከፍተኛ ደረጃ ተሸጋግሯል፡፡ የዛሬዉ የሕዝባችን ትግል የአገዛዙን የከፋፍሎ መግዛት ግንብ ንዶ በተባበረ መንፈስና በአንድ ድምፅ የጋራ ጠላቱ የወያኔ አገዛዝና አልጠግብ ባይ ዘራፊ መሪዎቹ ብቻ መሆናቸዉን በማያሻማ ቋንቋ ከሚገልፅበት ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱን በተግባር አሣይቷል፡፡ ለዚህ ደግሞ አስረኛ ወሩን የያዘዉ የኦሮሞ ሕዝብ የነፃነት ትግልና በጎንደር የተቀጣጠለዉና ወደሌሎችም የአማራ ክልል አካባቢዎች በፍጥነት የተዛመተዉ የአማራ ሕዝብ የነፃነት ትግል ተሣታፊዎች ያነሷቸዉ መሠረታዊ ጥያቄዎች፣…

Read More

የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶከኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባር ማዕከላዊ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫና የቀረበ ጥሪ_2016

Official ODF Logo

የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባር (ኦዲግ) ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ከሐምሌ 22 – 28 2008 ዓመተ ምህረት ድረስ ተካሂዷል፡፡ ይህን የአሁኑን የማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ልዩ የሚያደርገዉ የኦሮሞ ሕዝብ በመላዉ ኦሮሚያ በሚያስደንቅ የአንድነት፣ የቆራጥነትና የጀግንነት ስሜት እያካሄደ ያለዉንና ለዘጠኝ ወራት የዘለቀዉን የነፃነት፣ የዲሞክራሲ፣ የእኩልነት፣ የሰብዓዊ መብት እና ራሱን በራሱ የማስተዳደር ጥያቄዎቹን እጅግ አጠናክሮ በቀጠለበት ታሪካዊ ወቅት የተካሄደ መሆኑ ነዉ፡፡ የኦዲግ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት በመላዉ ኦሮሚያ የሚካሄደዉ ሰላማዊ የሕዝብ ተቃዉሞ በገዢዉ ቡድን የተደረጉበትንና የሚደረጉበትን አስከፊ ጫናዎችና የመሣሪያ አፈናዎች ሁሉ ተቋቁሞ ወደ ከፍተኛ ደረጃ እየተሸጋገረና በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ ሌሎች ኢትዮጵያዉያን ወገኖቹንም ለተመሣሣይ ትግል እያነሣሣ መሆኑን በአድናቆት እንመለከታለን፤ በሚቻለን መንገድ ሁሉም ለሰላማዊ ትግሉ ድጋፍ ለመስጠት ያለንን…

Read More

ODF Political Program (Amharic)

ODF Political Program

Please download the attachment to get the Amharic version of ODF’s Political Program. ODF Political Program (Amharic)

Read More

Declaration of The Oromo Democratic Front (ODF) – Amharic

ODF Begins

Please download the attachment to get the Amharic version of ODF’s Statement. Declaration of ODF in Amharic

Read More